# ማስታረቅ፣ ዕርቅ “ማስታረቅ” እና፣ “ዕርቅ” ቀድሞ እርስ በርስ ይጠላሉ በነበሩ ሰዎች መካከል፣ “ሰላም ማድረግ” ማለት ነው። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ይህ ቃል በልጁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ መሥዋዕት እግዚአብሔር ሰዎችን ከራሱ ጋር ማስታረቁን ያመለክታል። * በኀጢአት ምክንያት የሰው ልጆች ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ነበር። ከፍቅርና ርኅራኄው የተነሣ እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ሰዎች ከእርሱ ጋር የሚታረቁበትን መንገድ አዘጋጀ። * የኢየሱስ መሥዋዕት ለኀጢአታችን የተከፈለ ዋጋ መሆኑን በማመን ሰዎች ይቅርታን አግኝተው ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ይኖራቸዋል።