መዝሙር
ቅዱስ ዝማሬ፣ ብዙ ጊዜ በሙዚቃ የታጀበ ግጥም ወይም ቅኔ ማለት ነው። ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለው መጽሐፈ መዝሙር በእስራኤላውያን የተጻፉ የመዝሙሮች ስብስብ ይዟል።
- ሙሴና ንጉሥ ዳዊት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን ሲያመልኩ የሚጠቀሙባቸው መዝሙሮች ጽፈዋል።
- መዝሙራቶች እንደ ሐዘንና ጉዳት ሁሉ ደስታን፣ እምነትንና አክብሮትን ለመግለጥ ያገለግላሉ።
- በአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የአምልኮአቸው መገለጫ የሆኑ መዝሙሮች እንዲዘምሩ ተነግሮአቸዋል።