# መዝሙር ቅዱስ ዝማሬ፣ ብዙ ጊዜ በሙዚቃ የታጀበ ግጥም ወይም ቅኔ ማለት ነው። ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለው መጽሐፈ መዝሙር በእስራኤላውያን የተጻፉ የመዝሙሮች ስብስብ ይዟል። * ሙሴና ንጉሥ ዳዊት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን ሲያመልኩ የሚጠቀሙባቸው መዝሙሮች ጽፈዋል። * መዝሙራቶች እንደ ሐዘንና ጉዳት ሁሉ ደስታን፣ እምነትንና አክብሮትን ለመግለጥ ያገለግላሉ። * በአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የአምልኮአቸው መገለጫ የሆኑ መዝሙሮች እንዲዘምሩ ተነግሮአቸዋል።