am_tw/bible/kt/priest.md

14 lines
2.0 KiB
Markdown

# ካህን፣ ክህነት
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካህን ሕዝብን በመወከል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ነው። “ክህነት” እንዲህ ላለው ሰው ተግባር የተሰጠ ስም ወይም ቦታ ነው።
* ብሉይ ኪዳን ውስጥ ለእስራኤል ሕዝብ ካህናት እንዲሆኑ እግዚአብሔር አሮንና ልጆቹን መርጧል።
* “ክህነት” በሌዋውያን ነገድ ውስጥ ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፍ መብትና ኀላፊነት ነበር።
* የእስራኤል ካህናት ቤተ መቅደሱ ውስጥ ሌሎች ተግባሮችን መፈጸምን ጨምሮ የሕዝቡን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የማቅረብ ኀላፊነት ነበራቸው።
* ካህናት ለሕዝቡ ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩና ሌሎች ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን ይፈጽሙ ነበር።
* ካህናት ወግ ባለው መልኩ ሕዝቡን ይባርካሉ፤ የእግዚአብሔርን ሕጎች ያስተምራሉ።
* ኢየሱስ በዚህ ምድር ባገለገለበት ዘመን የካህናት አልቆችንና ሊቀ ካህኑን ጨምሮ የተለያዩ የካህናት ደረጃዎች ነበሩ።
* ኢየሱስ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ የሚማልድ፣ “ታላቅ ሊቀ ካህናችን” ነው። የመጨረሻው የኀጢአት መሥዋዕት ለመሆን ራሱን ሰጠ። ይህም ማለት ካህናት የሚያቀርቧቸው መሥዋዕቶች ከእንግዲህ አያስፈልጉም ማለት ነው።
* በአዲስ ኪዳን መሠረት በኢየሱስ የሚያምን እያንዳንዱ አማኝ “ካህን” ነው፤ ለሱና ለሌሎች ለመማለድ በጸሎት በቀጥጣ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይችላል።
* በጥንት ዘመን በአልን ለመሳሰሉ የሐሰት አማልክት መሥዋዕት የሚያቀርቡ አረማውያን ካህናትም ነበር።