am_tw/bible/kt/priest.md

2.0 KiB

ካህን፣ ክህነት

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካህን ሕዝብን በመወከል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ነው። “ክህነት” እንዲህ ላለው ሰው ተግባር የተሰጠ ስም ወይም ቦታ ነው።

  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ለእስራኤል ሕዝብ ካህናት እንዲሆኑ እግዚአብሔር አሮንና ልጆቹን መርጧል።
  • “ክህነት” በሌዋውያን ነገድ ውስጥ ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፍ መብትና ኀላፊነት ነበር።
  • የእስራኤል ካህናት ቤተ መቅደሱ ውስጥ ሌሎች ተግባሮችን መፈጸምን ጨምሮ የሕዝቡን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የማቅረብ ኀላፊነት ነበራቸው።
  • ካህናት ለሕዝቡ ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩና ሌሎች ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን ይፈጽሙ ነበር።
  • ካህናት ወግ ባለው መልኩ ሕዝቡን ይባርካሉ፤ የእግዚአብሔርን ሕጎች ያስተምራሉ።
  • ኢየሱስ በዚህ ምድር ባገለገለበት ዘመን የካህናት አልቆችንና ሊቀ ካህኑን ጨምሮ የተለያዩ የካህናት ደረጃዎች ነበሩ።
  • ኢየሱስ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ የሚማልድ፣ “ታላቅ ሊቀ ካህናችን” ነው። የመጨረሻው የኀጢአት መሥዋዕት ለመሆን ራሱን ሰጠ። ይህም ማለት ካህናት የሚያቀርቧቸው መሥዋዕቶች ከእንግዲህ አያስፈልጉም ማለት ነው።
  • በአዲስ ኪዳን መሠረት በኢየሱስ የሚያምን እያንዳንዱ አማኝ “ካህን” ነው፤ ለሱና ለሌሎች ለመማለድ በጸሎት በቀጥጣ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይችላል።
  • በጥንት ዘመን በአልን ለመሳሰሉ የሐሰት አማልክት መሥዋዕት የሚያቀርቡ አረማውያን ካህናትም ነበር።