# ካህን፣ ክህነት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካህን ሕዝብን በመወከል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ነው። “ክህነት” እንዲህ ላለው ሰው ተግባር የተሰጠ ስም ወይም ቦታ ነው። * ብሉይ ኪዳን ውስጥ ለእስራኤል ሕዝብ ካህናት እንዲሆኑ እግዚአብሔር አሮንና ልጆቹን መርጧል። * “ክህነት” በሌዋውያን ነገድ ውስጥ ከአባት ወደ ልጅ የሚተላለፍ መብትና ኀላፊነት ነበር። * የእስራኤል ካህናት ቤተ መቅደሱ ውስጥ ሌሎች ተግባሮችን መፈጸምን ጨምሮ የሕዝቡን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የማቅረብ ኀላፊነት ነበራቸው። * ካህናት ለሕዝቡ ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩና ሌሎች ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን ይፈጽሙ ነበር። * ካህናት ወግ ባለው መልኩ ሕዝቡን ይባርካሉ፤ የእግዚአብሔርን ሕጎች ያስተምራሉ። * ኢየሱስ በዚህ ምድር ባገለገለበት ዘመን የካህናት አልቆችንና ሊቀ ካህኑን ጨምሮ የተለያዩ የካህናት ደረጃዎች ነበሩ። * ኢየሱስ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ የሚማልድ፣ “ታላቅ ሊቀ ካህናችን” ነው። የመጨረሻው የኀጢአት መሥዋዕት ለመሆን ራሱን ሰጠ። ይህም ማለት ካህናት የሚያቀርቧቸው መሥዋዕቶች ከእንግዲህ አያስፈልጉም ማለት ነው። * በአዲስ ኪዳን መሠረት በኢየሱስ የሚያምን እያንዳንዱ አማኝ “ካህን” ነው፤ ለሱና ለሌሎች ለመማለድ በጸሎት በቀጥጣ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይችላል። * በጥንት ዘመን በአልን ለመሳሰሉ የሐሰት አማልክት መሥዋዕት የሚያቀርቡ አረማውያን ካህናትም ነበር።