am_tw/bible/kt/power.md

10 lines
1.1 KiB
Markdown

# ኀይል፣ ኀይላት
“ኀይል” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አብዛኛውን ጊዜ በታላቅ ብርታት ነገሮችን ማድረግን ወይም ነገሮች እንዲሆኑ የማድረግ ችሎታን ነው።
“ኀይላት” የሚያመለክተው ነገሮች እንዲሆኑ የማድረግ ታላቅ ችሎታ ያላቸው ሰዎችን ወይም መናፍስትን ነው።
* “የእግዚአብሔር ኀይል” ማንኛውንም ነገር በተለይም ለሰዎች የማይቻሉ ነገሮችን ለማድረግ እግዚአብሔር ያለውን ችሎታ ያመለክታል።
* እግዚአብሔር በፈጠረው ማንኛውም ነገር ላይ ፍጹም ኀይል አለው።
* እርሱ የሚፈልገውን እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለእሕዝቡ ኀይል ይሰጣል፤ ስለዚህ በሽተኞችን ሲፈውሱ ወይም ሌሎች ተአምራት ሲያደርጉ ያንን ያደረጉት በእግዚአብሔር ለይል ነው ማለት ነው።
* ኢየሱስና መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር በመሆናቸው ይኸው ኀይል አላቸው።