# ኀይል፣ ኀይላት “ኀይል” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አብዛኛውን ጊዜ በታላቅ ብርታት ነገሮችን ማድረግን ወይም ነገሮች እንዲሆኑ የማድረግ ችሎታን ነው። “ኀይላት” የሚያመለክተው ነገሮች እንዲሆኑ የማድረግ ታላቅ ችሎታ ያላቸው ሰዎችን ወይም መናፍስትን ነው። * “የእግዚአብሔር ኀይል” ማንኛውንም ነገር በተለይም ለሰዎች የማይቻሉ ነገሮችን ለማድረግ እግዚአብሔር ያለውን ችሎታ ያመለክታል። * እግዚአብሔር በፈጠረው ማንኛውም ነገር ላይ ፍጹም ኀይል አለው። * እርሱ የሚፈልገውን እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ለእሕዝቡ ኀይል ይሰጣል፤ ስለዚህ በሽተኞችን ሲፈውሱ ወይም ሌሎች ተአምራት ሲያደርጉ ያንን ያደረጉት በእግዚአብሔር ለይል ነው ማለት ነው። * ኢየሱስና መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር በመሆናቸው ይኸው ኀይል አላቸው።