am_tw/bible/kt/miracle.md

2.1 KiB

ተአምር፣ ድንቅ፣ ምልክት

“ተአምር”እግዚአብሔር ራሱ ካላደረገው በቀር ጨርሶ ሊሆን የማይችል አስደናቂ ነገር ነው።

  • ኢየሱስ ያደረጋቸው ተአምራት፣ ባሕርን ጸጥ ማሰኘትናን የዕውሩን ዐይን መክፈትንም ያካትታሉ።
  • ሰዎችን በመደነቅና በመገረም ስለሚሙ “ተአምራት” አንዳንዴ፣ “ድንቆች” ተብለው ይጠራሉ።
  • “ድንቅ” የሚለው ቃል አጠቃላይ በሆነ ሁኔታ የእግዚአብሔር ኀይልን መገለጥ ለምሳሌ፣ ሰማይና ምድርን በመፍጠር የተገለጠው ኀይሉን ያመለክታል።
  • የእግዚአብሔርን ኀያልነትና አጽናፈ ዓለሙ ላይ ያለውን ፍጹም ሥልጣን የሚያሳዩ ወይም ማስረጃ የሚሆኑ ከመሆናቸው የተነሣ ተአምራት፣ “ምልክቶች” ተብለውም ይጠራሉ።
  • የእስራኤልን ከግብፅ መውጣት፣ የዳንኤልን ከአንበሶች አፍ መዳን እንደ መሳሰሉት ነገሮች አንዳንድ ትአምራት የእግዚአብሔር ማዳን ሥራዎች ናቸው።
  • በኖኅ ዘመን በምድር ሁሉ ላይ የጥፋት ውሃ ማምጣቱን፣ በሙሴ ዘመን በግብፅ ምድር መቅሠፍት ማምጣቱን የመሳሰሉ ሌሎች ድንቆች የእግዚአብሔር ፍርድ ሥራዎች ናቸው።
  • አብዛኞቹ የእግዚአብሔር ተአምራት በሽተኞችን መፈሰስ ወይም የሞቱ ሰዎችን ማስነሣት ናቸው።
  • ሰዎችን ሲፈውስ፣ ባሕርን ጸጥ ሲያደርግ፣ በባሕር ሲራመድ፣ የሞቱ ሰዎችን ሲያስነሣ የእግዚአብሔር ኀይል በኢየሱስ አማካይነት ተገልጧ። አንዚህ ሁሉ ተአምራት ናቸው።
  • የፈውስ ተአምራትንና በእግዚአብሔር ኀይል ብቻ የሚቻሉ ነገሮችን እንዲያደርጉ ለነቢያትና ለሐዋርያት ተአምራት የማድረግ ችሎታን ሰጥቷቸው ነበር።