am_tw/bible/kt/miracle.md

14 lines
2.1 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ተአምር፣ ድንቅ፣ ምልክት
“ተአምር”እግዚአብሔር ራሱ ካላደረገው በቀር ጨርሶ ሊሆን የማይችል አስደናቂ ነገር ነው።
* ኢየሱስ ያደረጋቸው ተአምራት፣ ባሕርን ጸጥ ማሰኘትናን የዕውሩን ዐይን መክፈትንም ያካትታሉ።
* ሰዎችን በመደነቅና በመገረም ስለሚሙ “ተአምራት” አንዳንዴ፣ “ድንቆች” ተብለው ይጠራሉ።
* “ድንቅ” የሚለው ቃል አጠቃላይ በሆነ ሁኔታ የእግዚአብሔር ኀይልን መገለጥ ለምሳሌ፣ ሰማይና ምድርን በመፍጠር የተገለጠው ኀይሉን ያመለክታል።
* የእግዚአብሔርን ኀያልነትና አጽናፈ ዓለሙ ላይ ያለውን ፍጹም ሥልጣን የሚያሳዩ ወይም ማስረጃ የሚሆኑ ከመሆናቸው የተነሣ ተአምራት፣ “ምልክቶች” ተብለውም ይጠራሉ።
* የእስራኤልን ከግብፅ መውጣት፣ የዳንኤልን ከአንበሶች አፍ መዳን እንደ መሳሰሉት ነገሮች አንዳንድ ትአምራት የእግዚአብሔር ማዳን ሥራዎች ናቸው።
* በኖኅ ዘመን በምድር ሁሉ ላይ የጥፋት ውሃ ማምጣቱን፣ በሙሴ ዘመን በግብፅ ምድር መቅሠፍት ማምጣቱን የመሳሰሉ ሌሎች ድንቆች የእግዚአብሔር ፍርድ ሥራዎች ናቸው።
* አብዛኞቹ የእግዚአብሔር ተአምራት በሽተኞችን መፈሰስ ወይም የሞቱ ሰዎችን ማስነሣት ናቸው።
* ሰዎችን ሲፈውስ፣ ባሕርን ጸጥ ሲያደርግ፣ በባሕር ሲራመድ፣ የሞቱ ሰዎችን ሲያስነሣ የእግዚአብሔር ኀይል በኢየሱስ አማካይነት ተገልጧ። አንዚህ ሁሉ ተአምራት ናቸው።
* የፈውስ ተአምራትንና በእግዚአብሔር ኀይል ብቻ የሚቻሉ ነገሮችን እንዲያደርጉ ለነቢያትና ለሐዋርያት ተአምራት የማድረግ ችሎታን ሰጥቷቸው ነበር።