# ተአምር፣ ድንቅ፣ ምልክት “ተአምር”እግዚአብሔር ራሱ ካላደረገው በቀር ጨርሶ ሊሆን የማይችል አስደናቂ ነገር ነው። * ኢየሱስ ያደረጋቸው ተአምራት፣ ባሕርን ጸጥ ማሰኘትናን የዕውሩን ዐይን መክፈትንም ያካትታሉ። * ሰዎችን በመደነቅና በመገረም ስለሚሙ “ተአምራት” አንዳንዴ፣ “ድንቆች” ተብለው ይጠራሉ። * “ድንቅ” የሚለው ቃል አጠቃላይ በሆነ ሁኔታ የእግዚአብሔር ኀይልን መገለጥ ለምሳሌ፣ ሰማይና ምድርን በመፍጠር የተገለጠው ኀይሉን ያመለክታል። * የእግዚአብሔርን ኀያልነትና አጽናፈ ዓለሙ ላይ ያለውን ፍጹም ሥልጣን የሚያሳዩ ወይም ማስረጃ የሚሆኑ ከመሆናቸው የተነሣ ተአምራት፣ “ምልክቶች” ተብለውም ይጠራሉ። * የእስራኤልን ከግብፅ መውጣት፣ የዳንኤልን ከአንበሶች አፍ መዳን እንደ መሳሰሉት ነገሮች አንዳንድ ትአምራት የእግዚአብሔር ማዳን ሥራዎች ናቸው። * በኖኅ ዘመን በምድር ሁሉ ላይ የጥፋት ውሃ ማምጣቱን፣ በሙሴ ዘመን በግብፅ ምድር መቅሠፍት ማምጣቱን የመሳሰሉ ሌሎች ድንቆች የእግዚአብሔር ፍርድ ሥራዎች ናቸው። * አብዛኞቹ የእግዚአብሔር ተአምራት በሽተኞችን መፈሰስ ወይም የሞቱ ሰዎችን ማስነሣት ናቸው። * ሰዎችን ሲፈውስ፣ ባሕርን ጸጥ ሲያደርግ፣ በባሕር ሲራመድ፣ የሞቱ ሰዎችን ሲያስነሣ የእግዚአብሔር ኀይል በኢየሱስ አማካይነት ተገልጧ። አንዚህ ሁሉ ተአምራት ናቸው። * የፈውስ ተአምራትንና በእግዚአብሔር ኀይል ብቻ የሚቻሉ ነገሮችን እንዲያደርጉ ለነቢያትና ለሐዋርያት ተአምራት የማድረግ ችሎታን ሰጥቷቸው ነበር።