am_tw/bible/kt/manna.md

874 B

መና

መና ከግብፅ ከወቱ በኋላ እስራኤል በምድረ በዳ ይንከራተቱ በነበሩ ጊዜ እግዚአብሔር የሰጣቸው እንጀራ የመሰለ ስስ ምግብ ነበር።

  • መና በየጥዋቱ መሬት ላይ ካለው ጤዛ ነጭ ቅርፊት ይገኝ ነበር። ከሰንበት በቀር እስራኤላውያን በየዕለቱ ይሰበስቡት ነበር፤ ምን ጊዜም ሰውን ሁሉ ለመመገብ ይበቃ ነበር።
  • ከሰንበት በፊት በነበረው ቀን ሁለት ዕጥፍ መና መሰብሰብ እንዳለባቸው እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮ ነበር፤ እንዲህ የሚያደርጉት በሰንበት ቀን መሰብሰብ ስለማይገባ ነበር።
  • “መና” ማለት፣ “ይህ ምንድን ነው?” ማለት ነው።