# መና መና ከግብፅ ከወቱ በኋላ እስራኤል በምድረ በዳ ይንከራተቱ በነበሩ ጊዜ እግዚአብሔር የሰጣቸው እንጀራ የመሰለ ስስ ምግብ ነበር። * መና በየጥዋቱ መሬት ላይ ካለው ጤዛ ነጭ ቅርፊት ይገኝ ነበር። ከሰንበት በቀር እስራኤላውያን በየዕለቱ ይሰበስቡት ነበር፤ ምን ጊዜም ሰውን ሁሉ ለመመገብ ይበቃ ነበር። * ከሰንበት በፊት በነበረው ቀን ሁለት ዕጥፍ መና መሰብሰብ እንዳለባቸው እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተናግሮ ነበር፤ እንዲህ የሚያደርጉት በሰንበት ቀን መሰብሰብ ስለማይገባ ነበር። * “መና” ማለት፣ “ይህ ምንድን ነው?” ማለት ነው።