am_tw/bible/kt/humble.md

1.1 KiB

ትሑት፣ ትሕትና

ትሑት ሰው ከሌሎች ሁሉ የበለጠ እንደ ሆነ አያስብም። ትዕቢተኛ ወይም እብሪተኛ አይደለም።

  • በእግዚአብሔር ፊት ትሑት መሆን ከእርሱ ታላቅነት፣ ጥበብና ፍጽምና አንጻር የራሳችንን ደካማነትና ጉድለት መረዳት ማለት ነው።
  • አንድ ሰው ራሱን ትሑት ሲያደርግ፣ ራሱን ዝቅተኛው አስፈላጊነት ደረጃ ላይ ያኖራል።
  • ትሕትና ከራስ አስቀድሞ ስለ ሌሎች ችግር ማሰብ ማለት ነው።
  • ትሕትና ባሉን ስጦታዎችና ችሎታዎች ስንጠቀም ልከኛ በሆነ ዝንብሌ ማገልገል ማለት ነው።
  • “ትሑት ሁን” የሚለው ሐረግ፣ “ትዕቢተኛ አትሁን” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • “በእግዚአብሔር ፊት ትሑት ሁን” የሚለው፣ “የእርሱን ታላቅነት በመገንዘብ ፈቀድህን ለእርሱ አስገዛ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።