# ትሑት፣ ትሕትና ትሑት ሰው ከሌሎች ሁሉ የበለጠ እንደ ሆነ አያስብም። ትዕቢተኛ ወይም እብሪተኛ አይደለም። * በእግዚአብሔር ፊት ትሑት መሆን ከእርሱ ታላቅነት፣ ጥበብና ፍጽምና አንጻር የራሳችንን ደካማነትና ጉድለት መረዳት ማለት ነው። * አንድ ሰው ራሱን ትሑት ሲያደርግ፣ ራሱን ዝቅተኛው አስፈላጊነት ደረጃ ላይ ያኖራል። * ትሕትና ከራስ አስቀድሞ ስለ ሌሎች ችግር ማሰብ ማለት ነው። * ትሕትና ባሉን ስጦታዎችና ችሎታዎች ስንጠቀም ልከኛ በሆነ ዝንብሌ ማገልገል ማለት ነው። * “ትሑት ሁን” የሚለው ሐረግ፣ “ትዕቢተኛ አትሁን” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። * “በእግዚአብሔር ፊት ትሑት ሁን” የሚለው፣ “የእርሱን ታላቅነት በመገንዘብ ፈቀድህን ለእርሱ አስገዛ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።