9 lines
1.2 KiB
Markdown
9 lines
1.2 KiB
Markdown
|
# ያልተፈቀደ
|
||
|
|
||
|
“ያልተፈቀደ” ነገር የሚያደርግ ሰው ሕግ ያፈርሳል።
|
||
|
|
||
|
* አዲስ ኪዳን ውስጥ፣ “ያልተፈቀደ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው፣ የእግዚአብሔርን ሕግ ማፍረስን ብቻ ሳይሆን ሰው ሠራሽ የአይሁድ ሕግንም ለማፍረስ ጭምር ነው።
|
||
|
* በጊዜ ውስጥ አይሁድ እግዚአብሔር በሰጣቸው ሕግ ላይ የራሳቸውንም ጨምረዋል። ከእነርሱ ሰው ሠራሽ ሕግ ጋር የማይስማማውን አይሁድ፣ “ያልተፈቀደ” ይሉታል።
|
||
|
* ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በሰንበት ቀን እሸት ቀጥፈው በመብላታቸው፣ በዚያ ቀን ምንም ነገር እንዳይደረግ የደነገገውን የአይሁድ ሕግ ማፍረስ በመሆኑ፣ “ያልተፈቀደ” ብለውታል።
|
||
|
* ንጹሕ ያልሆነ ምግብ መብላት ለእርሱ፣ “ያልተፈቀደ” እንደ ነበር ጴጥሮስ ሲናገር ይህን ምግብ ከበላ አንዳንድ ምግቦችን እንዳይበሉ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የሰጠውን ሕግ ማፍረስ መሆኑን ማመልከቱ ነበር።
|