# ያልተፈቀደ “ያልተፈቀደ” ነገር የሚያደርግ ሰው ሕግ ያፈርሳል። * አዲስ ኪዳን ውስጥ፣ “ያልተፈቀደ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው፣ የእግዚአብሔርን ሕግ ማፍረስን ብቻ ሳይሆን ሰው ሠራሽ የአይሁድ ሕግንም ለማፍረስ ጭምር ነው። * በጊዜ ውስጥ አይሁድ እግዚአብሔር በሰጣቸው ሕግ ላይ የራሳቸውንም ጨምረዋል። ከእነርሱ ሰው ሠራሽ ሕግ ጋር የማይስማማውን አይሁድ፣ “ያልተፈቀደ” ይሉታል። * ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በሰንበት ቀን እሸት ቀጥፈው በመብላታቸው፣ በዚያ ቀን ምንም ነገር እንዳይደረግ የደነገገውን የአይሁድ ሕግ ማፍረስ በመሆኑ፣ “ያልተፈቀደ” ብለውታል። * ንጹሕ ያልሆነ ምግብ መብላት ለእርሱ፣ “ያልተፈቀደ” እንደ ነበር ጴጥሮስ ሲናገር ይህን ምግብ ከበላ አንዳንድ ምግቦችን እንዳይበሉ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የሰጠውን ሕግ ማፍረስ መሆኑን ማመልከቱ ነበር።