am_tw/bible/other/torment.md

10 lines
1.2 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ስቃይ
“ስቃይ” የሚያመለክተው ከፍተኛ መከራን ነው። አንድን ሰው ማሰቃየት ብዙውን ጊዜ በጭካኔ ከባድ መከራ እንዲደርስበት ማድረግ ነው።
* አንዳንዴ፣ “ስቃይ” አካላዊ ሕመምና መከራን ያመለክታል። ለምሳሌ፣ የዮሐንስ ራእይ አውሬውን በሚያመልኩ ሰዎች ላይ በመጨረሻው ዘመን ስለሚደርሰው ስቃይ ይገልጻል።
* መከራ ኢዮብ ላይ እንደ ደረሰው መንፈሳዊና ስሜታዊ ይዘት ሊኖረውም ይችላል።
* የዮሐንስ ራእይ እንደሚነግረን እንደ አዳኝ በኢየሱስ የማያምኑ ሰዎች የእሳት ባሕር ውስጥ ዘላለማዊ መንፈሳዊ ስቃይ ይቀበላሉ።
* ይህ ቃል፣ “ከባድ መከራ” ወይም፣ “አንድን ሰው በጣም ማሳመም ወይም፣ “ጭንቀት” በማለት መተርጎም ይቻላል።
* ትርጕሙን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ፣ “አካላዊ” ወይም፣ “መንፈሳዊ” የሚል ቃል መጨመር ያስፈልግ ይሆናል።