# ስቃይ “ስቃይ” የሚያመለክተው ከፍተኛ መከራን ነው። አንድን ሰው ማሰቃየት ብዙውን ጊዜ በጭካኔ ከባድ መከራ እንዲደርስበት ማድረግ ነው። * አንዳንዴ፣ “ስቃይ” አካላዊ ሕመምና መከራን ያመለክታል። ለምሳሌ፣ የዮሐንስ ራእይ አውሬውን በሚያመልኩ ሰዎች ላይ በመጨረሻው ዘመን ስለሚደርሰው ስቃይ ይገልጻል። * መከራ ኢዮብ ላይ እንደ ደረሰው መንፈሳዊና ስሜታዊ ይዘት ሊኖረውም ይችላል። * የዮሐንስ ራእይ እንደሚነግረን እንደ አዳኝ በኢየሱስ የማያምኑ ሰዎች የእሳት ባሕር ውስጥ ዘላለማዊ መንፈሳዊ ስቃይ ይቀበላሉ። * ይህ ቃል፣ “ከባድ መከራ” ወይም፣ “አንድን ሰው በጣም ማሳመም ወይም፣ “ጭንቀት” በማለት መተርጎም ይቻላል። * ትርጕሙን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ፣ “አካላዊ” ወይም፣ “መንፈሳዊ” የሚል ቃል መጨመር ያስፈልግ ይሆናል።