am_tw/bible/other/snare.md

13 lines
1.8 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ወጥመድ፣ አሽከላ
“ወጥመድ” እና፣ “አሽከላ” የተሰኙት ቃሎች እንስሶችን ለመያዝና ከዚያ እንዳያመልጡ ለመድረግ ጥቅም ላይ የሚውሉ ነገሮች ናቸው። የሚጠመደውን እንስሳ በድንገት እንደያዘው ብዙውን ጊዜ ወጥመዱ ወይም አሽክላው ድብቅ ቦታ ላይ ይቀመጣል
* በመንፈሳዊ መልኩ አንድን ሰው ማጥመድን አስመልክቶ እነዚህ ቃሎች በምሳሌነት ጥቅም ላይ ይውላሉ
* ብዙውን ጊዜ ወጥመድ እንስሳው ሲረግጠው እግሩን ለመያዝ በድንገት የሚጠብቅ የገመድ ወይም የሽቦ ሸምቀቆ ይኖረዋል
* ብዙውን ጊዜ ወጥመድ የሚሰራው ከብረት ወይም ከእንጨት ሲሆን የእንስሳውን አንድ አንድ አካል ክፍል በፍጥነትና በኅይል ለመያዝ እርስ በርስ የሚገጣጠሙ ሁለት ክፍሎች አሉት’
* ኅጢአትና ፈተና ሰዎችን እንደሚያጠምድ ወጥመድ መሆናቸውን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ በእነዚህ ቃሎች ይጠቅማል
* ሰዎች ኅጥአትን እንዲፈጽሙ ለማነሳሳት ሰይጣንና ክፉ ሰዎች ወጥመድ እንደሚዘረጉ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል
* “ወጥመድ መዘርጋት” ሌላውን ለመያዝ በፍጥነት እንዲዘጋ ወጥመድ ማዘጋጀት ማለት ነው
* “ወጥመድ ውስጥ መውደቅ” እንድ ሰው ውስጥ እንዲወድቅ ታስቦ የተቆፈረ ጉድጓድ ወይም ጉድባ ውስጥ መውደቅን ያመለክታል
* በኅጢአት ወጥመድ መያዝ ወይም መጠመድ አደገኛ ውጤት ያስከትላል