# ወጥመድ፣ አሽከላ “ወጥመድ” እና፣ “አሽከላ” የተሰኙት ቃሎች እንስሶችን ለመያዝና ከዚያ እንዳያመልጡ ለመድረግ ጥቅም ላይ የሚውሉ ነገሮች ናቸው። የሚጠመደውን እንስሳ በድንገት እንደያዘው ብዙውን ጊዜ ወጥመዱ ወይም አሽክላው ድብቅ ቦታ ላይ ይቀመጣል * በመንፈሳዊ መልኩ አንድን ሰው ማጥመድን አስመልክቶ እነዚህ ቃሎች በምሳሌነት ጥቅም ላይ ይውላሉ * ብዙውን ጊዜ ወጥመድ እንስሳው ሲረግጠው እግሩን ለመያዝ በድንገት የሚጠብቅ የገመድ ወይም የሽቦ ሸምቀቆ ይኖረዋል * ብዙውን ጊዜ ወጥመድ የሚሰራው ከብረት ወይም ከእንጨት ሲሆን የእንስሳውን አንድ አንድ አካል ክፍል በፍጥነትና በኅይል ለመያዝ እርስ በርስ የሚገጣጠሙ ሁለት ክፍሎች አሉት’ * ኅጢአትና ፈተና ሰዎችን እንደሚያጠምድ ወጥመድ መሆናቸውን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ በእነዚህ ቃሎች ይጠቅማል * ሰዎች ኅጥአትን እንዲፈጽሙ ለማነሳሳት ሰይጣንና ክፉ ሰዎች ወጥመድ እንደሚዘረጉ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል * “ወጥመድ መዘርጋት” ሌላውን ለመያዝ በፍጥነት እንዲዘጋ ወጥመድ ማዘጋጀት ማለት ነው * “ወጥመድ ውስጥ መውደቅ” እንድ ሰው ውስጥ እንዲወድቅ ታስቦ የተቆፈረ ጉድጓድ ወይም ጉድባ ውስጥ መውደቅን ያመለክታል * በኅጢአት ወጥመድ መያዝ ወይም መጠመድ አደገኛ ውጤት ያስከትላል