am_tw/bible/other/rebel.md

8 lines
820 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ማመፅ፣ ዐመፀኛ
ማመፅ ሥልጣን ላይ ላለ ሰው አለመገዛት ማለት ነው። ለአለቃ አለመታዘዝ ማለትም ነው።
* እነርሱ ላይ ሥልጣን ያላቸው እንዲያደርጉ ያዘዟቸውን ሰዎች ማድረግ ካልፈለጉ ልብ ውስጥ ዐመፅ ይፈጠራል።
* ሰዎች በቀጥታ ባለ ሥልጣኖችን ከተቃወሙ ወይም አንታዘዝም ካሉ በገሃድ የሚታይ ዐመፅ ይፈጠራል።
* ማመፅ የሚለው ቃል ንጉሣቸው ወይም መሪያቸው ላይ ጦርነት የሚያነሡ ሰዎችንም ይመለከታል። ሰዎች እንዲህ የሚያደርጉት ንጉሥ ወይ መሪው መሪው በትክክል እያስተዳደረ አይደለም በማለት ሲያስቡ ነው።