# ማመፅ፣ ዐመፀኛ ማመፅ ሥልጣን ላይ ላለ ሰው አለመገዛት ማለት ነው። ለአለቃ አለመታዘዝ ማለትም ነው። * እነርሱ ላይ ሥልጣን ያላቸው እንዲያደርጉ ያዘዟቸውን ሰዎች ማድረግ ካልፈለጉ ልብ ውስጥ ዐመፅ ይፈጠራል። * ሰዎች በቀጥታ ባለ ሥልጣኖችን ከተቃወሙ ወይም አንታዘዝም ካሉ በገሃድ የሚታይ ዐመፅ ይፈጠራል። * ማመፅ የሚለው ቃል ንጉሣቸው ወይም መሪያቸው ላይ ጦርነት የሚያነሡ ሰዎችንም ይመለከታል። ሰዎች እንዲህ የሚያደርጉት ንጉሥ ወይ መሪው መሪው በትክክል እያስተዳደረ አይደለም በማለት ሲያስቡ ነው።