am_tw/bible/other/obey.md

9 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መታዘዝ፣ ታዛዥ፣ ታዛዥነት
“መታዘዝ” ሥልጣን ያለው ሰው የሚፈልገውን ወይም እንዲደረግ የሚያዝዘውን መፈጸም ማለት ነው። “ታዛዥ” የተነገረውን ወይም የታዘዘውን የሚፈጽም ሰው ነው።
* ሰዎች የአገር መሪዎች መንግሥት ወይም ድርጅት ለሚያወጧቸው ሕጎችም ይታዘዛሉ።
* ልጆች ለወላጆቻቸው ይታዘዛሉ፣ ባርያዎች ለጌቶቻቸው ይታዘዛሉ፤ ሰዎች ለእግዚአብሔር ይታዘዛሉ፤ ዜጎች ለአገራቸው ሕጎችና ደንቦች ይታዘዛሉ።
* ሕጉ ወይም ሥልጣን ያለው ሰው አንድ ነገር እንዳይደረግ ካዘዙ፣ ሰዎች ያንን ላለማድረግ መታዘዝ አልባቸው።
* ይህን ቃል ለመተርጎም የሚጠቅሙ ቃሎች ወይም ሐረጎች፣ “የታዘዘውን ማድረግ” ወይም፣ “ትእዛዙን መከተል” ወይም፣ “እግዚአብሔር የተናገረውን ማድረግ” የተሰኙትንም ያካትታል።