# መታዘዝ፣ ታዛዥ፣ ታዛዥነት “መታዘዝ” ሥልጣን ያለው ሰው የሚፈልገውን ወይም እንዲደረግ የሚያዝዘውን መፈጸም ማለት ነው። “ታዛዥ” የተነገረውን ወይም የታዘዘውን የሚፈጽም ሰው ነው። * ሰዎች የአገር መሪዎች መንግሥት ወይም ድርጅት ለሚያወጧቸው ሕጎችም ይታዘዛሉ። * ልጆች ለወላጆቻቸው ይታዘዛሉ፣ ባርያዎች ለጌቶቻቸው ይታዘዛሉ፤ ሰዎች ለእግዚአብሔር ይታዘዛሉ፤ ዜጎች ለአገራቸው ሕጎችና ደንቦች ይታዘዛሉ። * ሕጉ ወይም ሥልጣን ያለው ሰው አንድ ነገር እንዳይደረግ ካዘዙ፣ ሰዎች ያንን ላለማድረግ መታዘዝ አልባቸው። * ይህን ቃል ለመተርጎም የሚጠቅሙ ቃሎች ወይም ሐረጎች፣ “የታዘዘውን ማድረግ” ወይም፣ “ትእዛዙን መከተል” ወይም፣ “እግዚአብሔር የተናገረውን ማድረግ” የተሰኙትንም ያካትታል።