am_tw/bible/other/lute.md

9 lines
906 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ክራር፣ መሰንቆ
ክራርና መሰንቆ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ለማምለክት የሚጠቀሙባቸው ትናንሽ ባለ ገመድ የሙዚቃ መሣሪያዎች ናቸው።
* መሰንቆ ክሮቹ የሚወጠሩበት ቀዳዳ ያሉት በመሆኑ በጣም በገናን ይመስላል።
* ክራር የድምፅ እንጨት ሳጥንና ክሮቹ የሚወጠሩበት ረዘም ያለ አንገት ስላለው በብዙ መልኩ የዘመኑን ጊታር ይመስላል።
* ክራር ወይም መሰንቆ ለመጫወት ሲፈለግ አንዳንድ ክሮች ጫን ተደርገው በጣቶች ሲያዙ፣ ሌሎች ደግም በሌላ እጅ ይመታሉ።
* የክሮቹ ቁጥር የተለያየ ቢሆንም፣ ብሉይ ኪዳን በተለይ አሥር ክሮች (አውታር) ስላሉት መሣሪያዎች ይናገራል።