# ክራር፣ መሰንቆ ክራርና መሰንቆ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን ለማምለክት የሚጠቀሙባቸው ትናንሽ ባለ ገመድ የሙዚቃ መሣሪያዎች ናቸው። * መሰንቆ ክሮቹ የሚወጠሩበት ቀዳዳ ያሉት በመሆኑ በጣም በገናን ይመስላል። * ክራር የድምፅ እንጨት ሳጥንና ክሮቹ የሚወጠሩበት ረዘም ያለ አንገት ስላለው በብዙ መልኩ የዘመኑን ጊታር ይመስላል። * ክራር ወይም መሰንቆ ለመጫወት ሲፈለግ አንዳንድ ክሮች ጫን ተደርገው በጣቶች ሲያዙ፣ ሌሎች ደግም በሌላ እጅ ይመታሉ። * የክሮቹ ቁጥር የተለያየ ቢሆንም፣ ብሉይ ኪዳን በተለይ አሥር ክሮች (አውታር) ስላሉት መሣሪያዎች ይናገራል።