am_tw/bible/other/interpret.md

10 lines
1.4 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መተርጎም፣ ትርጉም
“መተርጎም” እና፣ “ትርጉም” የተሰኙት ግልጽ ያልሆነ ነገርን መርዳትና ያንን ግልጽ ማድረግን ያመለክታል።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እነዚህ ቃሎች ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት የሕልምን ፍቺ ግልጽ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ነው።
* የባቢሎን ንጉሠአንዳንድ ግራ የሚያጋቡ ሕልሞች ባለመ ጊዜ ምን ማለት እንደሆኑ እንዲተረጉምና ግልጽ እንዲያደርግ እግዚአብሔር ዳንኤልን ረዳው።
* የሕልሙ “ትርጉም”፣ የሕልሙን መልእክት ግልጽ ማድረግ ነው። አንዳንዴ እነዚህ ትርጉሞች በጽሑፍ ይሰፍራሉ።
* ከብሉይ ኪዳን እንደምንመለከተው ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር ወደፊት የሚሆኑ ነገሮችን ለሰዎች በሕልም ይገልጽ ነበር፤ ስለሆነም የእነዚህ ሕልሞች ትርጉም ትንቢት ነበር ማለት ነው።
* “መተርጎም” የሚለው ቃል በተፈጥሮአዊው ዓለም እየሆን ያለውን መሠረት በማድረግ የአየሩ ሁኔታ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመትን የመሰለ የአንዳንድ ነገሮችን ምንነት መገመትን ለምግለጽም ጥቅም ላይ ይውላል።