# መተርጎም፣ ትርጉም “መተርጎም” እና፣ “ትርጉም” የተሰኙት ግልጽ ያልሆነ ነገርን መርዳትና ያንን ግልጽ ማድረግን ያመለክታል። * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እነዚህ ቃሎች ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት የሕልምን ፍቺ ግልጽ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ነው። * የባቢሎን ንጉሠአንዳንድ ግራ የሚያጋቡ ሕልሞች ባለመ ጊዜ ምን ማለት እንደሆኑ እንዲተረጉምና ግልጽ እንዲያደርግ እግዚአብሔር ዳንኤልን ረዳው። * የሕልሙ “ትርጉም”፣ የሕልሙን መልእክት ግልጽ ማድረግ ነው። አንዳንዴ እነዚህ ትርጉሞች በጽሑፍ ይሰፍራሉ። * ከብሉይ ኪዳን እንደምንመለከተው ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር ወደፊት የሚሆኑ ነገሮችን ለሰዎች በሕልም ይገልጽ ነበር፤ ስለሆነም የእነዚህ ሕልሞች ትርጉም ትንቢት ነበር ማለት ነው። * “መተርጎም” የሚለው ቃል በተፈጥሮአዊው ዓለም እየሆን ያለውን መሠረት በማድረግ የአየሩ ሁኔታ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመትን የመሰለ የአንዳንድ ነገሮችን ምንነት መገመትን ለምግለጽም ጥቅም ላይ ይውላል።