am_tw/bible/names/zerubbabel.md

10 lines
903 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ዘሩባቤል
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ዘሩባቤል ተብለው የተጠሩ ሁለት ሰዎች ነበር።
* ከእነዚህ አንዱ የኢዮአቄምና የሴዴቅያስ ዘር ነበር።
* የሰላይታል ልጅ ተብሎ የሚጠራው ሌላው ዘሩባቤል የባቢሎን ምርኮኞች እየተመለሱ በነበረበት አንዱ ጉዞ የይሁዳ ነገድ አለቃ ሆኖ የነበረው ነው።
* ይኸኛው ዘሩባብል የነበረው የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እስራኤላውያን ከባቢሎን ምርኮ ነጻ እንዲወጡ ባደረገበት ዘመን ነበር።
* ዘሩባቤልና ሊቀ ካህኑ ኢያሱ ቤተ መቅደስና የእግዚአብሔር መሠዊያ ሲሠራ ከረዱት መካከል ነበር።
* ዘሩባቤል የነበረው ዕዝራና ነህምያ በነበሩበት ዘመን ነበር።