# ዘሩባቤል ብሉይ ኪዳን ውስጥ ዘሩባቤል ተብለው የተጠሩ ሁለት ሰዎች ነበር። * ከእነዚህ አንዱ የኢዮአቄምና የሴዴቅያስ ዘር ነበር። * የሰላይታል ልጅ ተብሎ የሚጠራው ሌላው ዘሩባቤል የባቢሎን ምርኮኞች እየተመለሱ በነበረበት አንዱ ጉዞ የይሁዳ ነገድ አለቃ ሆኖ የነበረው ነው። * ይኸኛው ዘሩባብል የነበረው የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እስራኤላውያን ከባቢሎን ምርኮ ነጻ እንዲወጡ ባደረገበት ዘመን ነበር። * ዘሩባቤልና ሊቀ ካህኑ ኢያሱ ቤተ መቅደስና የእግዚአብሔር መሠዊያ ሲሠራ ከረዱት መካከል ነበር። * ዘሩባቤል የነበረው ዕዝራና ነህምያ በነበሩበት ዘመን ነበር።