am_tw/bible/names/succoth.md

9 lines
1.0 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ሱኮት
ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሱኮት ተብለው የተጠሩ ሁለት ከተሞች አሉ። ሱኮት “መጠለያ” ወይም፣ “መጠጊያ” ማለት ነው
* ሱኮት ተብላ የተጠራችው የመጀመሪያዋ ከተማ ከዮርዳኖስ ወንዝ ምሥራቅ ትገኝ ነበር
* ያዕቆብ ከቤተ ሰቡ እና ከነበሩት የቤት እንስሳት ጋር በሱኮት ቆዩ፤ በዚያም መጠጊያ መጠለያ ሠራላቸው
* ከመቶ ዓመታት በኋላ ጌዴዎንና ተዳክመው የነበሩት አብረውት ያሉ ሰዎች ምድያማውያንን እያሳደዱ በነበረ ጊዜ በሱኮት ቆይታ አድርገው ነበር፤ እዚያ የነበሩ ሰዎች ግን ምግብ እንኳ ሊሰጧቸው አልፈለጉም
* ሁለተኛዋ ሱኮት የምትገኘው በሰሜናዊ የግብፅ ድንበር ሲሆን ከግብፅ ባርነት አምልጠው ቀይ ባሕርን ከተሻገሩ በኋላ ካረፉባቸው ቦታዎች አንዷ ነበረች