# ሱኮት ብሉይ ኪዳን ውስጥ ሱኮት ተብለው የተጠሩ ሁለት ከተሞች አሉ። ሱኮት “መጠለያ” ወይም፣ “መጠጊያ” ማለት ነው * ሱኮት ተብላ የተጠራችው የመጀመሪያዋ ከተማ ከዮርዳኖስ ወንዝ ምሥራቅ ትገኝ ነበር * ያዕቆብ ከቤተ ሰቡ እና ከነበሩት የቤት እንስሳት ጋር በሱኮት ቆዩ፤ በዚያም መጠጊያ መጠለያ ሠራላቸው * ከመቶ ዓመታት በኋላ ጌዴዎንና ተዳክመው የነበሩት አብረውት ያሉ ሰዎች ምድያማውያንን እያሳደዱ በነበረ ጊዜ በሱኮት ቆይታ አድርገው ነበር፤ እዚያ የነበሩ ሰዎች ግን ምግብ እንኳ ሊሰጧቸው አልፈለጉም * ሁለተኛዋ ሱኮት የምትገኘው በሰሜናዊ የግብፅ ድንበር ሲሆን ከግብፅ ባርነት አምልጠው ቀይ ባሕርን ከተሻገሩ በኋላ ካረፉባቸው ቦታዎች አንዷ ነበረች