am_tw/bible/names/paul.md

12 lines
1.5 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ጳውሎስ፣ ሳውል
ጳውሎስ ለሌሎች ብዙ ሕዝቦች የምሥራቹን ቃል እንዲያደርስ ኢየሱስ የላከው የጥንት ቤተ ክርስቲያን መሪ ነበር።
* ጳውሎስ ጠርሴስ በምትባል የሮም ከተማ የተወለደ አይሁዳዊ ሲሆን፣ የሮም ዜግነትም ነበረው።
* ጳውሎስ መጀመሪያ ይጠራ የነበረው ሳውል በተባለ አይሁዳዊ ስሙ ነበር።
* ጳውሎስ የአይሁድ ሃይማኖት መሪ ሆነ፤ እርሱ በኢየሱስ የማያምን ሰው ስለ ነበር ክርስቲያን የሆኑትን አይሁዳውያን ያስር ነበር።
* ኢየሱስ በታላቅ ብርሃን ወደ ሳውል መጥቶ ክርስቲያኖችን ማሳደዱን እንዲያቆም ነገረው። ከዚያም ኢየሱስ ሳውልን እንዲያስተምረው አንድ ክርስቲያን ሰው ላከ፤ ጳውሎስም በኢየሱስ አመነ።
* መጀመሪያ ላይ ሳውል ለአይሁድ ስለ ኢየሱስ ማስተማር ጀመረ።
* በኋላም በተለያዩ የሮም ከተሞች ለነበሩ ሰዎች ስለ ኢየሱስ እንዲያስተምር እግዚአብሔር ሳውልን ላከው። በዚያ ጊዜ ጳውሎስ በተሰኘ ሮማዊ ስም መጠራት ጀመረ።
* ጳውሎስ በተለያዩ ከተሞች የነበሩ ክርስቲያኖችን ለማበረታታትና ለማስተማር መልእክቶች ጻፈ። መልእክቶቹም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ።