# ጳውሎስ፣ ሳውል ጳውሎስ ለሌሎች ብዙ ሕዝቦች የምሥራቹን ቃል እንዲያደርስ ኢየሱስ የላከው የጥንት ቤተ ክርስቲያን መሪ ነበር። * ጳውሎስ ጠርሴስ በምትባል የሮም ከተማ የተወለደ አይሁዳዊ ሲሆን፣ የሮም ዜግነትም ነበረው። * ጳውሎስ መጀመሪያ ይጠራ የነበረው ሳውል በተባለ አይሁዳዊ ስሙ ነበር። * ጳውሎስ የአይሁድ ሃይማኖት መሪ ሆነ፤ እርሱ በኢየሱስ የማያምን ሰው ስለ ነበር ክርስቲያን የሆኑትን አይሁዳውያን ያስር ነበር። * ኢየሱስ በታላቅ ብርሃን ወደ ሳውል መጥቶ ክርስቲያኖችን ማሳደዱን እንዲያቆም ነገረው። ከዚያም ኢየሱስ ሳውልን እንዲያስተምረው አንድ ክርስቲያን ሰው ላከ፤ ጳውሎስም በኢየሱስ አመነ። * መጀመሪያ ላይ ሳውል ለአይሁድ ስለ ኢየሱስ ማስተማር ጀመረ። * በኋላም በተለያዩ የሮም ከተሞች ለነበሩ ሰዎች ስለ ኢየሱስ እንዲያስተምር እግዚአብሔር ሳውልን ላከው። በዚያ ጊዜ ጳውሎስ በተሰኘ ሮማዊ ስም መጠራት ጀመረ። * ጳውሎስ በተለያዩ ከተሞች የነበሩ ክርስቲያኖችን ለማበረታታትና ለማስተማር መልእክቶች ጻፈ። መልእክቶቹም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ።