1.5 KiB
1.5 KiB
ጳውሎስ፣ ሳውል
ጳውሎስ ለሌሎች ብዙ ሕዝቦች የምሥራቹን ቃል እንዲያደርስ ኢየሱስ የላከው የጥንት ቤተ ክርስቲያን መሪ ነበር።
- ጳውሎስ ጠርሴስ በምትባል የሮም ከተማ የተወለደ አይሁዳዊ ሲሆን፣ የሮም ዜግነትም ነበረው።
- ጳውሎስ መጀመሪያ ይጠራ የነበረው ሳውል በተባለ አይሁዳዊ ስሙ ነበር።
- ጳውሎስ የአይሁድ ሃይማኖት መሪ ሆነ፤ እርሱ በኢየሱስ የማያምን ሰው ስለ ነበር ክርስቲያን የሆኑትን አይሁዳውያን ያስር ነበር።
- ኢየሱስ በታላቅ ብርሃን ወደ ሳውል መጥቶ ክርስቲያኖችን ማሳደዱን እንዲያቆም ነገረው። ከዚያም ኢየሱስ ሳውልን እንዲያስተምረው አንድ ክርስቲያን ሰው ላከ፤ ጳውሎስም በኢየሱስ አመነ።
- መጀመሪያ ላይ ሳውል ለአይሁድ ስለ ኢየሱስ ማስተማር ጀመረ።
- በኋላም በተለያዩ የሮም ከተሞች ለነበሩ ሰዎች ስለ ኢየሱስ እንዲያስተምር እግዚአብሔር ሳውልን ላከው። በዚያ ጊዜ ጳውሎስ በተሰኘ ሮማዊ ስም መጠራት ጀመረ።
- ጳውሎስ በተለያዩ ከተሞች የነበሩ ክርስቲያኖችን ለማበረታታትና ለማስተማር መልእክቶች ጻፈ። መልእክቶቹም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛሉ።