am_tw/bible/names/jonah.md

11 lines
826 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ዮናስ
ዮናስ በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረ እስራኤላዊ ነቢይ ነበር።
* እግዚአብሔር ዮናስን ወደነነዌ የላከው መቼ እንደነበር ትንቢተ ዮናስ ይናገራል።
* ወደነነዌ እንዲሄድና ሕዝቡ ከኀጢአት እንዲመለሱ እንዲናገር እግዚአብሔር ለዮናስ ነገረው።
* ዮናስ ግን አልታዘዘም ወደሌላ አገር ለመሄድ መርከብ ተሳፈረ።
* መርከቡ ላይ የነበሩ ሰዎች ዮናስን ወደባሕር ጣሉት፣ አንድ ትልቅ ዓሣ ዮናስን ዋጠው።
* ዮናስ ሥስት ቀን በዓሣ ሆድ ውስጥ ነበር።
* ዮናስ ወደነነዌ ሄደ ለሕዝቡ ሰበከ፤ እነርሱም ከኀጢአታቸው ተመለሱ።