# ዮናስ ዮናስ በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረ እስራኤላዊ ነቢይ ነበር። * እግዚአብሔር ዮናስን ወደነነዌ የላከው መቼ እንደነበር ትንቢተ ዮናስ ይናገራል። * ወደነነዌ እንዲሄድና ሕዝቡ ከኀጢአት እንዲመለሱ እንዲናገር እግዚአብሔር ለዮናስ ነገረው። * ዮናስ ግን አልታዘዘም ወደሌላ አገር ለመሄድ መርከብ ተሳፈረ። * መርከቡ ላይ የነበሩ ሰዎች ዮናስን ወደባሕር ጣሉት፣ አንድ ትልቅ ዓሣ ዮናስን ዋጠው። * ዮናስ ሥስት ቀን በዓሣ ሆድ ውስጥ ነበር። * ዮናስ ወደነነዌ ሄደ ለሕዝቡ ሰበከ፤ እነርሱም ከኀጢአታቸው ተመለሱ።