am_tw/bible/names/hittite.md

10 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ኬጢያዊ
ኬጢያውያን በልጁ በከነዓን በኩል የካም ዘሮች ነበር። በአሁኑ ዘመን ቱርክ በሚባለውና ከፐስቲና በስተ ሰሜን ባለው አካባቢ ታላቅ መንግሥት ሆነው ነበር።
* በሥጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ ደረጃ ኬጢያውያን ሁሌም ለእስራኤል ስጋት ነበሩ።
* የሞተችው ሚስቱ ሣራን እዚያ በነበረ ዋሻ ውስጥ መቅበር እንዲችል አብርሃም ከኬቲያዊው ኤፍሮን ርስት ገዛ። የኋላ ኋላ አብርሃምና ከዘሮቹ ብዙዎቹ የተቀበሩት በዚያ ዋሻ ነበር።
* ሁለት ኬቲያውያን ሴቶች ባገባ ጊዜ የኤሳው ወላጆች አዝነው ነበር።
* ከዳዊት ኀያላን ሰዎች አንዱ ኬጢያዊው ኦርዮን ነበር።
* ከሰሎሞን ባዕዳን ሚስቶች አንዳንዶቹ ኬጢያውያን ነበር። እነርሱ ያመልኳቸው ከነበሩ ሐሰተኛ አማልክት የተነሣ እነዚህ ሴቶች የሰሎሞንን ልብ እግዚአብሔርን ከማምለክ መለሱት።