# ኬጢያዊ ኬጢያውያን በልጁ በከነዓን በኩል የካም ዘሮች ነበር። በአሁኑ ዘመን ቱርክ በሚባለውና ከፐስቲና በስተ ሰሜን ባለው አካባቢ ታላቅ መንግሥት ሆነው ነበር። * በሥጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ ደረጃ ኬጢያውያን ሁሌም ለእስራኤል ስጋት ነበሩ። * የሞተችው ሚስቱ ሣራን እዚያ በነበረ ዋሻ ውስጥ መቅበር እንዲችል አብርሃም ከኬቲያዊው ኤፍሮን ርስት ገዛ። የኋላ ኋላ አብርሃምና ከዘሮቹ ብዙዎቹ የተቀበሩት በዚያ ዋሻ ነበር። * ሁለት ኬቲያውያን ሴቶች ባገባ ጊዜ የኤሳው ወላጆች አዝነው ነበር። * ከዳዊት ኀያላን ሰዎች አንዱ ኬጢያዊው ኦርዮን ነበር። * ከሰሎሞን ባዕዳን ሚስቶች አንዳንዶቹ ኬጢያውያን ነበር። እነርሱ ያመልኳቸው ከነበሩ ሐሰተኛ አማልክት የተነሣ እነዚህ ሴቶች የሰሎሞንን ልብ እግዚአብሔርን ከማምለክ መለሱት።