am_tw/bible/names/hannah.md

9 lines
784 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ሐና
ሐና ብሉይ ኪዳኑ ውስጥ የነቢዩ ሳሙኤል እናት ናት። ከሕልቃና ሚስቶች አንዷ ነበረች።
* ሐና ልጅ መውለድ አለመቻልዋ ከባድ ሐዘን ሆኖባት ነበር።
* ሐና እግዚአብሔር ወንድ ልጅ አንዲሰጣት ቤተ መቅደስ ውስጥ አጥብቃ ጸለየች፣ ያ ልጅ ለእግዚአብሔር አገልግሎት እንደሚለይም ቃል ገባች።
* እግዚአብሔር የለመነችውን ሰጣት፤ ሕፃኑ ሳሙኤል ካደገ በኋላ በካህኑ በዔሊ መሪነት ሥር ቤተ መቅደስ ውስጥ እንዲያገለግል አመጣችው።
* ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ለሐና ሌሎች ልጆችንም ሰጥቷታል።