# ሐና ሐና ብሉይ ኪዳኑ ውስጥ የነቢዩ ሳሙኤል እናት ናት። ከሕልቃና ሚስቶች አንዷ ነበረች። * ሐና ልጅ መውለድ አለመቻልዋ ከባድ ሐዘን ሆኖባት ነበር። * ሐና እግዚአብሔር ወንድ ልጅ አንዲሰጣት ቤተ መቅደስ ውስጥ አጥብቃ ጸለየች፣ ያ ልጅ ለእግዚአብሔር አገልግሎት እንደሚለይም ቃል ገባች። * እግዚአብሔር የለመነችውን ሰጣት፤ ሕፃኑ ሳሙኤል ካደገ በኋላ በካህኑ በዔሊ መሪነት ሥር ቤተ መቅደስ ውስጥ እንዲያገለግል አመጣችው። * ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ለሐና ሌሎች ልጆችንም ሰጥቷታል።