am_tw/bible/names/caesarea.md

10 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ቄሳርያ፣ ፊልጶስ ቂሳርያ
ቂሳርያ ሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ፣ ከቀርሜሎስ ተራራ 39 ኪ.ሜ. ርቃ ትገኝ የነበረች በጣም ጠቃሚ ከተማ ነበረች። ፊልጶስ ቂሳርያ ከእስራኤል ሰሜን ምሥራቃዊ ክፍል አርሞንዔም ተራራ አጠገብ ያለች ከተማ ነበረች።
* እነዚህ ከተሞች የሮም መንግሥትን ይገዙ ለነበሩ ቄሳሮች የተሰየሙት።
* ኢየሱስ በተወለደበት ዘመን አካባቢ ባሕር ዳርቻ የነበረው ቂሳርያ የይሁዳ የሮም አውራጃ ከተማ ሆነች።
* ሐዋርያው ጴጥሮስ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአሕዛብ የሰበከው በቂሳርያ ነበር።
* ጳውሎስ ከቂሳርያ በመርከብ ወደ ጤርሴስ ሄደ፤ በሁለተኛው ሐዋርያዊ ተልዕኮው በዚህች ከተማ ሁለት ጊዜ አልፏል።
* ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በፊልጶስ ቂሳርያ ዙሪያ ወደ ነበሩ ከተሞች ተጉዘው ነበር።