# ቄሳርያ፣ ፊልጶስ ቂሳርያ ቂሳርያ ሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ፣ ከቀርሜሎስ ተራራ 39 ኪ.ሜ. ርቃ ትገኝ የነበረች በጣም ጠቃሚ ከተማ ነበረች። ፊልጶስ ቂሳርያ ከእስራኤል ሰሜን ምሥራቃዊ ክፍል አርሞንዔም ተራራ አጠገብ ያለች ከተማ ነበረች። * እነዚህ ከተሞች የሮም መንግሥትን ይገዙ ለነበሩ ቄሳሮች የተሰየሙት። * ኢየሱስ በተወለደበት ዘመን አካባቢ ባሕር ዳርቻ የነበረው ቂሳርያ የይሁዳ የሮም አውራጃ ከተማ ሆነች። * ሐዋርያው ጴጥሮስ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአሕዛብ የሰበከው በቂሳርያ ነበር። * ጳውሎስ ከቂሳርያ በመርከብ ወደ ጤርሴስ ሄደ፤ በሁለተኛው ሐዋርያዊ ተልዕኮው በዚህች ከተማ ሁለት ጊዜ አልፏል። * ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በፊልጶስ ቂሳርያ ዙሪያ ወደ ነበሩ ከተሞች ተጉዘው ነበር።