10 lines
1.2 KiB
Markdown
10 lines
1.2 KiB
Markdown
|
# አርጤክስስ
|
||
|
|
||
|
አርጤክስስ ከ 464-424 ዓቅክ የፋርስን መንግሥት ሲገዛ የነበረ ንጉሥ ነው
|
||
|
|
||
|
* በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት ከይሁዳ የተወሰዱት እስራኤላውያን በዚያ ጊዜ በፋርስ ቁጥጥር ሥር በነበረችው በባቢሎን ምርኮ ውስጥ ነበሩ
|
||
|
* ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ለእስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲያስተምሩ አርጤክስስ ለካህኑ ዕዝራና አብረውት ለነበሩ አይሁድ መሪዎች አርጤክስስ ፈቃድ ሰጠ
|
||
|
* በዚሁ ጊዜ ጥቂት ቆየት ብሎ ከተማዋን የሚከብበውን ቅጥር የሚሠሩ አይሁድን እየመሩ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ አርጤክስስ ለወይን ጠጅ አሳላፊው ለነህምያ ፈቃድ ሰጥቷል
|
||
|
* በዚያን ጊዜ ባቢሎን በፋርስ አገዛዝ ሥር ስለነበርች አንዳንዴ አርጤክስስ “የባቢሎን ንጉሥ” ተብሎ ይጠራል
|
||
|
* አርጤክስስ አሐሻዊሮስ ከሚባለው ሰው ጋር አንድ እንዳይደለ ልብ በሉ
|