# አርጤክስስ አርጤክስስ ከ 464-424 ዓቅክ የፋርስን መንግሥት ሲገዛ የነበረ ንጉሥ ነው * በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት ከይሁዳ የተወሰዱት እስራኤላውያን በዚያ ጊዜ በፋርስ ቁጥጥር ሥር በነበረችው በባቢሎን ምርኮ ውስጥ ነበሩ * ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ለእስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲያስተምሩ አርጤክስስ ለካህኑ ዕዝራና አብረውት ለነበሩ አይሁድ መሪዎች አርጤክስስ ፈቃድ ሰጠ * በዚሁ ጊዜ ጥቂት ቆየት ብሎ ከተማዋን የሚከብበውን ቅጥር የሚሠሩ አይሁድን እየመሩ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመለሱ አርጤክስስ ለወይን ጠጅ አሳላፊው ለነህምያ ፈቃድ ሰጥቷል * በዚያን ጊዜ ባቢሎን በፋርስ አገዛዝ ሥር ስለነበርች አንዳንዴ አርጤክስስ “የባቢሎን ንጉሥ” ተብሎ ይጠራል * አርጤክስስ አሐሻዊሮስ ከሚባለው ሰው ጋር አንድ እንዳይደለ ልብ በሉ