am_tq/3jn/01/01.md

831 B

በዚህ ደብዳቤ፣ ጸሐፊው ዮሐንስ ራሱን የሚያስተዋውቀው በምን ዓይነት መጠሪያ ነው?

ዮሐንስ ራሱን የሚያስተዋውቀው እንደ ሽማግሌ ነው

ዮሐንስ ይህንን ደብዳቤ ከሚቀበለው ከጋይዮስ ጋር ምን ዓይነት ዝምድና ነበረው ?

ዮሐንስ ጋይዮስን በእውነት ይወደዋል

ጋይዮስን በሚመለከት ዮሐንስ የሚጸልየው ስለ ምንድነው?

ጋይዮስ ነፍሱ እንደሚከናወንለት ጤና እንዲኖረውና በነገር ሁሉ እንዲከናወንለት ዮሐንስ ይጸልያል

የዮሐንስ ታላቁ ደስታው ምንድነው?

የዮሐንስ ታላቁ ደስታው ልጆቹ በእውነት እንደሚሄዱ መስማት ነው