# በዚህ ደብዳቤ፣ ጸሐፊው ዮሐንስ ራሱን የሚያስተዋውቀው በምን ዓይነት መጠሪያ ነው? ዮሐንስ ራሱን የሚያስተዋውቀው እንደ ሽማግሌ ነው # ዮሐንስ ይህንን ደብዳቤ ከሚቀበለው ከጋይዮስ ጋር ምን ዓይነት ዝምድና ነበረው ? ዮሐንስ ጋይዮስን በእውነት ይወደዋል # ጋይዮስን በሚመለከት ዮሐንስ የሚጸልየው ስለ ምንድነው? ጋይዮስ ነፍሱ እንደሚከናወንለት ጤና እንዲኖረውና በነገር ሁሉ እንዲከናወንለት ዮሐንስ ይጸልያል # የዮሐንስ ታላቁ ደስታው ምንድነው? የዮሐንስ ታላቁ ደስታው ልጆቹ በእውነት እንደሚሄዱ መስማት ነው