am_tn/psa/108/011.md

24 lines
1.5 KiB
Markdown

# አጠቃላይ መረጃ
እነዚህ ቁጥሮች በመዝሙር 60፡10-12 ካሉት ጥቅሶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው፣ ነገር ግን እንደ 60፡10 ጅማሬ መዝሙር 108:11 “ግን አንተ” የሚል ሐረግ እንደሌለው ልብ በሉ፡፡
# እግዚአብሔር ሆይ፣ የጣልኸን አንተ አይደለህምን?
መዝሙረኛው ልክ እግዚአብሔር እንደ ጣላቸው ለመግለጽ ይህንን ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ “ልክ እንደ ጣልኸን ይመስላል!” ወይም “እግዚአብሔር ሆይ ፣ አንተ የተውኸን ይመስላል!”
# ከሠራዊታችን ጋር ወደ ውጊያ አትወጣም
መዝሙረኛው፣ እግዚአብሔር የእነርሱን ሠራዊት እንዲረዳ የሚናገረው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ እንዲዋጋ ነው፡፡ “ወደ ጦርነት በሄድን ጊዜ ሠራዊታችንን አላገዝክም”
# ከንቱ ነው
“ዋጋ ቢስ ነው”
# ያሸንፋል
“ጠላቶቻችንን ያሸንፋል”
# ጠላቶቻችንን ይረግጣል
መዝሙረኛው፣ እግዚአብሔር ሠራዊታቸውን እንደሚረዳ ጠላቶቻቸውንም እንደሚያሸንፍ ወደ ታችም እንደሚረግጣቸው ይናገራል፡፡ “ጠላቶቻችንን እንድንረግጥ ይረዳናል” ወይም “ጠላቶቻችንን ማሸነፍ እንድንችል ያደርገናል።