am_tn/psa/108/011.md

1.5 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እነዚህ ቁጥሮች በመዝሙር 60፡10-12 ካሉት ጥቅሶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው፣ ነገር ግን እንደ 60፡10 ጅማሬ መዝሙር 108:11 “ግን አንተ” የሚል ሐረግ እንደሌለው ልብ በሉ፡፡

እግዚአብሔር ሆይ፣ የጣልኸን አንተ አይደለህምን?

መዝሙረኛው ልክ እግዚአብሔር እንደ ጣላቸው ለመግለጽ ይህንን ጥያቄ ይጠቀማል፡፡ “ልክ እንደ ጣልኸን ይመስላል!” ወይም “እግዚአብሔር ሆይ ፣ አንተ የተውኸን ይመስላል!”

ከሠራዊታችን ጋር ወደ ውጊያ አትወጣም

መዝሙረኛው፣ እግዚአብሔር የእነርሱን ሠራዊት እንዲረዳ የሚናገረው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ እንዲዋጋ ነው፡፡ “ወደ ጦርነት በሄድን ጊዜ ሠራዊታችንን አላገዝክም”

ከንቱ ነው

“ዋጋ ቢስ ነው”

ያሸንፋል

“ጠላቶቻችንን ያሸንፋል”

ጠላቶቻችንን ይረግጣል

መዝሙረኛው፣ እግዚአብሔር ሠራዊታቸውን እንደሚረዳ ጠላቶቻቸውንም እንደሚያሸንፍ ወደ ታችም እንደሚረግጣቸው ይናገራል፡፡ “ጠላቶቻችንን እንድንረግጥ ይረዳናል” ወይም “ጠላቶቻችንን ማሸነፍ እንድንችል ያደርገናል።